Your cart is currently empty!
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥዎች (የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከፎቶ ኮፒና ከኦሪጅናል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ አርዕስት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ቢድ ቦንድ /በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሰርቲፋይድ ቼክ CPO/ ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ ቀርበው በመውሰድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚሸጡበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒውን በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን በኮሚቴ መከፈት አያግደውም፡፡ የሚከበሩ የህዝብ በዓላት ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ቀበሌ 13 አዲስ ካስገነባው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
ስልክ ቁጥር፡- 058-2-22-19-99/ 058-2-20-19-70
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን
cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Vehicle (garage service) cttx, Electromechanical and Electronics cttx