የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

የጨረታ ቁጥር 07/2018 /

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ 2018 . የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፤

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስራት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።

6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን ግልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት ለግልባጭ መኪና በሜኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ግቢ በማድረግ የባን ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን – 09/02/2018 . ጀምሮ እስከ – 24/02/2018 . ዋናው /ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ – 09/02/2018 . 800 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 24/02/2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 830 ሰዓት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

11. የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመልክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድረ ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ

ባህር ዳር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *