Your cart is currently empty!
የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የመለያ ቁጥር፡- 01/2018 ዓ.ም.
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ሎት 1 – የደንብ ልብስ፡- 30,000
- ሎት 2 – አላቂ የፅዳት ዕቃ፦ 20,000
- ሎት 3 – አላቂ የቢሮ እቃ፡- 10,000
- ሎት 4- ኮምፒውተር ፎቶ ኮፒና ጥገና፡- 5,000
- ሎት 5 – ህትመት ባነር፡- 1,000
- ሎት 6 – አላቂ የትምህርት ዕቃ፡- 10,000
- ሎት 7 – አላቂ ህክምና እቃዎች ፡- 3,000
- ሎት 8 – የደንብ ልብስ ማሰፊያ፡- 1,000
- ሎት 9 – ፕላንትና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ፦ 30,000
- ሎት 10 – ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፡ 5,000
- ሎት 11 – ለህንጸና ለቁሳቁስ እና ተገጣጠሚዎች እድሣትና ኮንክሬትናሊሽ 10,000
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO) ካሽ ሪሴስተር ተመዘጋብ የሆኑ / ያለው ብቻ ነው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድና ኮፒ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 02 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በዓየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቆየው ለo(በአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ከአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችለሉ፡፡
- የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከት/ቤቱ ከገዙት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ሞልተው ከላይ በተራ ቁጥር አራት በተገለፀው መሰረት ጨረታው በአየር ላይ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በስራ ሰዓት በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰውን ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ በዋለ 11 / በአስራ አንደኛው / ቀን በጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉቸውን ዕቃዎች የግዥ መጠየቂያ (purchase order) ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ እቃውን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚጠይቁ እቃዎች ናሙና ማቅረብ እና ናሙና ለመቅረብ የሚያስቸግሩ እቃዎችን በፎቶ ግራፍና በዝርዝር መግለጫዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማስያዣ ሲፒኦ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ባቀረበው ዕቃ ውሉ ሳይቀየር ከተጫራች ጋር በመስማማት እስከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-8-93-16-37/ 011-8-93-16-37 ወይም በአካል በአንዶዴ
2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በመምጣት ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስረዳደር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Materials cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Pharmaceutical Products cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx