Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የብስክሌት ጥገና አገልግሎት እና የብስክሌት ስልጠና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ ት/ቢ/ግጨ/02/2018 በሎት 1 (አንድ) የብስክሌት ጥገና አገልግሎት እና በሎት 2 (ሁለት) የብስክሌት ስልጠና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ11፡00 ሰዓት በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (አንድ) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እና ለሎት 2 (ሁለት) ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- መገናኛ ስሪ ኤም ሲቲ ሞል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 011 639-46-55/ 011 639-30-10 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ