የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 02/18

መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተርና ሮለር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው በተለያ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፍል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።

4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።

5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ማሽን ብር 100,000.00/አንድ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው ላይ በተፈቀደ አቅራቢው በሚፈልገው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
የስልክ ቁጥር 0916866262/0461315012
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *