Your cart is currently empty!
ፈያ ኢንተርግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን Water Treatment Chemical በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
bid of no BID No FIDO/ 0025/2025
ድርጅታችን ፈያ ኢንተርግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ላለፉት 22 ዓመታት በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ከመንግስትና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን እየሰራ ያለ ህጋዊ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ከUNOCHA_EHF ባገኘነው Integrated multi-sector Lifesaving Humanitarian Assistance for People Affected by Critical Malnutrition and Education needs in Diga and Kiramu Woredas of East Wollega Zare ( Oromia Region, Ethiopia ድርጅታችን ከዚህ በታች የተገለፀውን ስራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የስራው አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Water Treatment Chemical
|
49,320 Sachets
|
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሁሉም አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በድርጅታችን (ፈያ ኢንተግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን) ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በታች ያስያዘ ከጨረታው ዉድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል።
- ስለጨረታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ሰባት (7) ቀናት ከፈያ ኢንትግሬትድ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ዋናው መስሪያ ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም (wax) በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙና ጨረታው በመኪፈትበት ቀን እና ሰዓት ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 9፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ኣሸናፊው ተጫራች ባሸነፈበት ዋጋ ያሸነፈበትን የእቃ ዝርዝር ውል በገባ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብና ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ውጤት) በኋላ የሚመለስ ይሆናል
- ተጫራቾች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ: አልሳም የመኖርያ መንደር _ ለፊት ከኢትዮካናዳ ክሊኒክ አጠገብ
- ስልክ ቁጥር፦ +251 – 11 557-81-14