Your cart is currently empty!
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የጽህፈት ቤቱ ግቢ ኮሪደር /ግቢውን የማስዋብ ሥራ/ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ኮሪደር ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የጽ/ቤቱ ግቢ ኮሪደር /ግቢውን የማስዋብ ሥራ/ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ኮሪደር ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።
1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የማከራየት ፈቃድ ያላቸው ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው ሆነው ኮሪደር ሥራ ላይ ከዚህ በፊት የሠሩበት የስራ ልምድ ያላቸው፤
2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሠርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ከሊራንስ አንዲሁም ከመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪናዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ /የውል ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።
4. ተጫራቹ ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት /ቴክኒክ/ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ኦሪጅናል ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ 1% በተጫራቹ የተሞላ የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ዋጋ /በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና /bank guarantee/ ወይም የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከመጫረቻ ሰነድ ወይም የቴክኒካል ዶከመንት ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
6.ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የሥራ ቦታ /site/ በራሳቸው ወጭ አይተው /visit/ ማረጋገጥ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፈቃዳቸውና ተ.ዕ.ታ VAT/የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ከሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 /ሀያ/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ/ ብር በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ገቢዎች ባ ቅ/ጽ/ ቤት በመከፈል ሰነዱን መወሰድ ይችላሉ።
8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ /security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻ ታሽጎ በትልቁ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁለቱም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አግልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ ። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- 0910740670/0916 651 155/0989 925 580
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት