Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
በአራዳ ከ/ከተማ ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ ማህበራት የተደራጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።
ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
|
ተ.ቁ
|
የስራው አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ዋ ስትና |
ደረጃ
|
የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1
|
በአራዳ ከ/ከተማ ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ የተለያዩ የጥገና ስራዎች |
10,000 ብር ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
|
በጥቃቅንና አነስተኛ ታዳጊ እና መብቃት
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30- 10፡30 ሰዓት
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ |
በጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
2. በዘርፉ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በአራዳ ክፍለ ከተማ ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው ሠነዱን 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
6. ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 የሚከፈትይሆናል።
7. ማንኛውም ተጫራቾች ለ60 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / BD BOND /በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (unConditional Bank Guarantee) ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (instruction to Bidder(TB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።
2. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
3. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ጤና ጣቢያው ባስገነባቸው ግንባታዎችም ሆነ እድሳቶች ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
5. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።
6.ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።
7. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 4ኛፎቅ የመስሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈስጉ አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 251 11 126 53 33 ደውለው መረዳት ይቻላል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ