በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ተሽከርካሪ ወይም ሞተር ሳይክል፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የህንፃ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ሥራ ጉዳይ የሚውል የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ሎቶች መወዳደር ይችላሉ።

  • ሎት 1 አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት 2 ተሽከርካሪ ወይም ሞተር ሳይክል
  • ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 4 የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች ሲሆኑ ከላይ በተጠቀሱ ሎቶች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

የተጫራቾች መመሪያ

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ቲን ካርድ፤የንግድ ም/ም/ወረቀት፤አቅራቢነት ም/ም/ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ኦሪጅናልና ሁለት የኦሪጅናል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ፣ የሚወዳደሩበት ሎት እና የድርጅቱ ማህተም በትክክል ተደርጎ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን መክተት ይኖርበታል።

3. ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታ ማግለል አይችልም።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ / ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርበታል።

5. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ሰንበት /በዓል/ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች በገዛ ፈቃዳቸው በጨረታ ቦታ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከገሱባ ከተማ አሰ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ግዥ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላል።

8. ለአሸናፊው ተጫራች በደብዳቤ ከተገለፀ በሶስት ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ብቻ በማቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል።

9. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን እስከ ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ አድርሶ ያስረክባል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0996 234 024/0910 726 453 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
አድራሻ፦ ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
በደ/ ኢት/ ክ / መ /በወላይታ ዞን ገሱባ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት