የአክሲዮን የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ወ/ሮ ቀለሟ ማሞ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ጌትነት ማሞ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/325139 በ26/6/2017 ዓ.ም እና 18/11/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለማስፈጸም ኤኤም ማተሚያ እና ማሸጊያ ድርጅት ኃ/የተ/የግ/ማህብር ውስጥ የፍ/ባለዕዳዎች ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ አቶ ጌትነት ማሞ 313 ወ/ሮ መዓዛ ማሞ 157፤ ወ/ሮ መቅደስ ማሞ 1571 አቶ ሳምሶን ማሞ 156 አጠቃላይ የፍ/ባለዕዳዎች የአክሲዮን ድርሻ 783 የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1,000 ሲሆን አጠቃላይ የፍ ባለዕዳዎች የአክሲዮን ዋጋ 783,000 (ሰባት መቶ ሰማኒያ ሦስት ሺህ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙቡቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለሙቡቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ኢያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት በ 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆን አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናል የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ግንብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ /አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ 15ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ  ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው  በልዩነት ቢሮ እንደሚሆን በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ  ሰለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም

ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *