የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጀት (ኢኢግልድ) የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ configuration እና ስልጠና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢኢግልድ 004/2018

ለድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጀት (ኢኢግልድ) የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ configuration እና ስልጠና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣

የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከድርጅቱ ግዢ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ ከconfiguration እና ስልጠና የአገልግሎት ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ከኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ፒያሳ ከሊፋ ሕንፃ አካባቢ በስተስሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ) አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2።

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ፦በስልክ ቁጥር 0111-57-24-97 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጀት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *