Your cart is currently empty!
በአብክመ ግብርና ቢሮ ዋናውን ቢሮ እድሳት ለማሰራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC‐5/BC-4 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ግብርና ቢሮ ዋናውን ቢሮ እድሳት ለማሰራት በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC‐5/BC-4 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም
1. ደረጃቸው GC-5/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በሥራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገቡና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን እና በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ መሆን አለባቸው፤
5. በክልሉ እና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል።
6. የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን በመውሰድ ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ፋይናንሺል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ከአንድ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የማይቻል ሲሆን ተጫራች በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ የሚሳተፍበትን ሎት በግልፅ በመጥቀስ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፣ የኦሪጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት።
9. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከዋለበት በኋላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ዓ.ም የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ120 ቀናት የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና መቅረብ አይቻልም።
|
ሎት |
የስራ ቦታ |
የስራው አይነት |
ጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
|
01 |
አብክመ ግብርና ቢሮ |
የ1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ወለል ዕድሳት ስራ |
350,000.00 |
|
02 |
አብክመ ግብርና ቢሮ |
የግራውንድ ወለል ዕድሳት ስራ |
300,000.00 |
|
03 |
አብክመ ግብርና ቢሮ |
የመሰብሰብያ አዳራሽ ዕድሳት ስራ |
500,000.00 |
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– +251-05-82-26-28-01 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት