በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ዋና ቅርንጫፍ በ2018 የበጀት ዓመት የፅህፈት እቃዎች (እስቴሽነሪ)፣ የጽዳት እቃዎች እና የቧንቧ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ዋና ቅርንጫፍ በ2018 የበጀት ዓመት የፅህፈት እቃዎች (እስቴሽነሪ)፣ የጽዳት እቃዎች እና የቧንቧ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ አንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

የጨረታ መመሪያ፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ Tin ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ሰነዱን ይሀ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መፃፍ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች 3% ዊዝሆልዲንግ መከፈል አለባቸው።
  8. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
  9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ ሲቀርቡ /ለመሳተፍ/ሙሉ የኦዲት ሪፖርት የ2017 ዓ.ም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ (Price Validity date) ከጨረታው መክፈቻ አለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበት ጊዜ 120 /አንድ መቶ ሀያ ቀናት (delivery time) ውስጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልቶ ካላቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱን የአቅራቢው ድርጅት ነው።
  13. ድርጅቱ የሚያጫርታቸውን እቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
  14. የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኃላ ነው። አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተነሳስቶ በፍፁም አይችልም።
  15. የሚቀርበው ዋጋ በሙሉ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  16. ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
  17. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ሳይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀር ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆንና አስፈላጊው ህጋዊ የሆነ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
  18. ተጫራቾች የቧንቧ ዕቃዎችን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ከሚያቀርቡት ፋብሪካ ላይ የዕቃውን ካታሎግ ማቅረብ አለባቸው።
  19.  የፅዳት እቃዎች ለእያንዳንዱ እቃ በተጠየቀው መሠረት ናሙና መቅረብ አለበት።
  20. ተጫራቹ ካሁን በፊት በጨረታ ከተሳተፈባቸው የመንግስትና የግል ድርጅቶች የዕውቅና ሠርተፊኬት ማቅረብ አለበት።
  21. በጨረታው ለግዢ የቀረቡ እቃዎች በሙሉ ጋራንትድ መሆን አለባቸው።
  22. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው 20,000 ሀያ ሺህ/ ብር አሸናፊው አካል ዕቃውን አስገብቶ እስኪጨርስ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
  23. ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ለውል ማስከበሪያ ያሲዛል እቃውን ሙሉ በሙሉ የማያቀርብ ከሆነ የውል ማስከበሪያው የማይመለስ ይሆናል።
  24. ማንኛውም ተጫራች የቧንቧ ዕቃዎች ላይ ጨረታውን ካሸነፈ የውሃ ፈንድ 0.5% የሚከፍል ይሆናል።

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ