አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የአደጋ መከላከያና ደንብ ልብስ ዕቃዎች፣ የንጽሕና መጠበቂያ እቃዎች እና የተሽከርካሪ ጥገና ለከባድ፣ ለቀላልና ለማሽነሪ ጋራዥ አገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን

ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ አላቂ እቃዎች እና

የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/03/2018

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1. የአደጋ መከላከያና ደንብ ልብስ ዕቃዎች
  • ሎት 2. የንጽሕና መጠበቂያ እቃዎች
  • ሎት 3 የተሽከርካሪ ጥገና ለከባድ፣ ለቀላልና ለማሽነሪ ጋራዥ አገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራከሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማስልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1፣ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2፣ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 3፤ 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guaranties) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ

ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከሲ.አር.ዲ.ኤ አጠገብ

ስልክ ቁጥር 011 4 62 14 57 / 0928742121

ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *