Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የጠጠር መንገድ ሥራ ለመሥራት ሰሌክት ማቴሪያል ግዥ ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የጠጠር መንገድ ሥራ ለመሥራት ሰሌክት ማቴሪያል ግዥ ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ድርጅት መወዳደር ይችላሉ።
- ኮንስት/ ማቴሪያል አቅራቢነት ዘርፍ፤
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደርህንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (አስር) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ወስዳችሁ ዋጋ ሞልታችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046-220-9963/ 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ልማት መምሪያ