Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ከተማ አ/ስ/ፋ/ኢ/ል መምሪያ የኤሌክትሪክ ኬብል /electric cable/ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አ/ስ/ፋ/ኢ/ል መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ካቀዳቸው ሥራዎች አንዱ የመንገድ መብራት ጥገና በመሆኑ ለዚህ አገልግሎት የሚሆን የኤሌክትሪከ ኬበል /electric cable/ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- 4.1 የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር – 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት
- ጨረታ ሰነዱ በስም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት – በፋይ/ኢል/ሚ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ – ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተዋሃደ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ።
- ተጫራች ጨረታ ስያስገቡ ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መም/ያ
ሀዋሳ