Your cart is currently empty!
የቤቱ ስፋት 75.59 ካ.ሜ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ዘበነ ሐጎስ እና በፍ ባለዕዳ ወ/ሮ ትዕግስት ብሩ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 196281 በ21/9/2017 ዓ.ም እና በመ/ቁ 209445 በ20/10/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በቀድሞው ወረዳ 01 በአዲሱ ወረዳ 13 ጀሞ 1 የሚገኝ ኮንዶሚኒየም በአቶ ዘበነ ሐጎስ ስም የተመዘገበ መለያ ቁጥር AA0000801045651650323 የቤት ቁጥር 165/23 የቤቱ ስፋት 75.59 ካ.ሜ የሆነ ባለ ሶስት ክፍል ኮንዶሚኒየም የሆነ መኖሪያ ቤት የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,386,362.21 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከ21 ሳንቲም ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራቾች በሚጫረቱበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታው ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት