የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ እና ሰሜን አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለቢሮ ኪራይ አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ እና ሰሜን አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

ስለዚህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፡-

  • ከአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት እስከ አዲሱ ገበያ በዋና ዋና መስመሮች፤
  • ከግንፍሌ አንስቶ ፒያሳ አትክልት ተራ ድረስ ባለው አካባቢ በዋና ዋና መስመሮች፤
  • ከአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት እስከ እምቢልታ ሆቴል ድረስ በዋና ዋና መስመሮች፤
  • ከዩኒቲ ፓርክ እስከ ካዛንቺስ ቅኡራኤል ቤተ ክርስቲያን፤
  • ከቅ/እስጢፋኖስ እስከ ቅኡራኤል ቤተ ክርስቲያን፤
  • ከአያት ሪጀንሲ ሆቴል እስከ ቦሌ ድረስ፤ 

የቢሮ ኪራይ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ያላችሁ ግለሰቦችና ድርጅቶች የምታከራዩበትን ዋጋ እና የኪራይ አከፋፈል ሁኔታን ጭምር በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘውና ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

በተጨማሪም አከራዮች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አስር ቀናት ውስጥ ካዛንችስ በሚገኘው ሾንጌ ህንጻ 1ኛ ወለል በአካል በመምጣት የህንጻውን ተስማሚነት በባንኩ ባለሙያ እንድታስማሙ ባንኩ ያሳስባል።

ኪራይ የሚቀርቡ ህንጻዎች፡-

1. የቢሮ ስፋት ለዲስትሪክቱ 226.5 ሜካ፣ ለቅርንጫፎች ለእያንዳንዳቸው 180.5 ሜ.ካ ያላነሰ መሆን ይኖርበታል።

2. ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀና መሠረተ ልማት በተሟላ ሁኔታ ያላቸው

3. ቢያንስ ለአምስት መኪኖች መቆሚያ ፓርኪንግ ያለው፤

4. የኪራይ ዘመኑ ቢያንስ 3 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ኮፒና የታደሰ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ ሰነድ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

6. ጨረታውን ያሸነፈ ጨረታውን ማሸነፉ ከተነገረው ቀን ጀምሮ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ የውል ስምምነት ተፈራርሞ ህንጻውን ማስረከብ አለበት።

7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስቁ 0115 57 72 33

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *