የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ደንብ ልብሶች ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ደንብ ልብሶች  ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

..

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ሣጥን የሚታሸግበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

የግዥ መለያ ቁጥር

1

የተለያዩ የደንብ ልብሶች

 

 

ጥቅምት 27 ቀን 2018 ..  ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት

ጥቅምት 27 ቀን 2018 ..  ከጠዋቱ 4:05 ሰዓት

DBE/NCB/U/G/001/2025/26

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

.

ዝርዝር

አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር

1

የዝናብ ልብስ

ጥራት ያለው

30,000.00 .... (CPO)  ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ህጋዊ ከሆነ ባንክ

2

የሾፌሮች ቱታ

3

ተከፋች የፅዳት  ካፖርት

4

ሻሽ ረጅም

5

ሻሽ አጭር

6

ጃንጥላ

1.    ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶችን ያቀርባሉ፡

  • የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት
  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /T.I.N/
  • የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ
  • በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ (ጊዜውያላላፈበት መሆን ይኖርበታል)
  • የተ.እ.ታክስ /VAT/ ሰርተፊኬት
  • የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት
  • የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት ፎርም

2. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር/ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ብር ሁለት መቶ/ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ ሁለት በባንኩ እግረኛ መግቢያ ክፍያውን ፈጽመው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገባ ብሎ በኪያሜድ ህንፃ (የቀድሞ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና/መቤት የነበረው) አንደኛ ፎቅ ከግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሶፍት ኮፒ በኢ-ሜይል ወይንም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. የጨረታ ሰነድ ለተጫራቾች መሸጥ የሚጀምረው ከጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካልና የዋጋ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ በሰንጠረዥ እስከ ተገለፀው ቀን እና ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገባ ብሎ ኪያሜድ ህንፃ (የቀድሞ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና/መቤት የነበረው) በሚገኘው የግዥ ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን የቴክኒካልና የፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5. አሸናፊው ተጫራች በተፈለገው ጥራት የደንብ ልብሱን ገቢ ካላደረገ ባንኩ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ በመሆኑ ተጫራቾች ይህንን በመገንዘብ ከጨረታ መክፈቻ ሰዓት በፊት የሚወዳደሩባቸውን የናሙና አይነቶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. የጨረታ ሰነዱ ቋንቋ አማርኛ ነው፡፡ ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገባ ብሎ ኪያሜድ ህንፃ (የቀድሞ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና/መቤት የነበረው) በሚገኘው የግዥ ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 557 8088 የውስጥ መስመር 378 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *