የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኤክስካቫተር ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት /እታ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዘት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

የጨረታ መዝጊያ

የጨረታ መክፈቻ

ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ

ቀን

ሰዓት

ቀን

ሰዓት

1

ኤክስካቫተር ማሽን

01/03/2018 ዓ.ም

4፡00

01/03/2018 ዓ.ም

4፡30

ሎጀስቲክስና ፕሮኪዩርመንት ዳይሬክቶሬት ክፍል

በዚሁ መሠረት ከላይ ለተገለፀው ግዥ ተጫራቾች ለሚወዳደሩብት የግዥ ዓይነት በዘርፉ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ በአቅራቢነት ድረ-ገፅ (Website) ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸው ከቢዎችና ጉምሩከ ባለስልጣን የሚሰጥ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንዲሣተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች የእያንዳንዱን የሚወዳደሩበትን ጨረታ ሠነድ ላይ የተሰለጸውን የዕቃውን/የአገልግሎት/ ዝርዝር መግለጫ መሠረት በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በሎጀስቲክስና ፕሮኪዩርመንት ዳይሬክቶሬት ብሎክ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒዎችን ለየብቻው በትልቅ ፖስታ በማሸግና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተወዳዳሩባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በኮርፖሬሽኑ ስም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ 3 በግንባር በመቅረብ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ ኮርፖሬሽኑ የሚገኘው 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ሆቴል ገባ ብሎ ብሎክ ቁጥር 3 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09-38-72-45-89 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *