የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቅይጥ አገልግሎት የሚሆን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ

የሐራጅ መነሻ

ዋጋ (ብር) /

የጨረታው ቀን

 

አድራሻ

 

የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር

የይዞታው ስፋት (ካሜ)

የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎቱ

1

ጉጂ ሃይላንድ ኮፊ ፕላንቴሽን .የተ.የግ.ማህበር

ወይ እቴነሽ መለሰ ፈንቴ

አዲስ አበባ ከተማ የካ /ከተማ

AA00005 1207950

380

 

ቅይጥ አገልግሎት

 

16,053,645.36

 

16/03/2018 .ጠዋት 300-400

 

በመሆኑም፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
  2. የንብረቱ ጨረታ የሚከናወነዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በሚገኘዉ አዳራሽ ቁጥር 4203 ነው።
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
  4. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
  5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
  6. ንብረቱ ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
  7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊ ስለመሆኑ የሚገልጽ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  8. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱ ካልተረከበ ከንብረቱ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
  9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስ..011-113-05-08 ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና /ቤት 42 ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *