የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ አንድ (1) የሆኑ የሀገር ውስጥ እና የሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ የመንገድ ሥራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የዶሎ አዶ አየር ማረፊያ የምህንድስና ዲዛይን፣ የጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ SSNT-T7579

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ አንድ (1) የሆኑ የሀገር ውስጥ እና የሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ የመንገድ ሥራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የዶሎ አዶ አየር ማረፊያ የምህንድስና ዲዛይን፣ የጨረታ ሰነድ ዝግጅት፣ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በዶሎ አዶ ከተማ ይገኛል።
  2. አማካሪነት አገልግሎት ሥራው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ዲዛይን በ5 ወራት ውስጥ, ለግንባታ ቁጥጥር እና ኮንትራት አስተዳደር በ15 ወራት ውስጥ ማጠናቀቅ እና አንድ ዓመት ከትትል ጊዜ (Defect liability period) ይሆናል።
  3. ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾችስ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ለ2017 ዓ.ም የታደሰ በመንገድ ሥራ ማማከር አገልግሎት ደረጃ-1 የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T579 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy)፣ የድርጅቱን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-

ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴከኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ +251 11-517-8918

ኢ-ሜይል፦ ESAYASTS@ethopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *