Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ የህግ ማሠልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት በአዳማ ከተማ ከአባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል በስተምእራብ በኩል ባለው ዋና ጽህፈት ቤት ሕንፃ ውስጥ ያሉት ሁለት አሳንሰሮች (ሊፍቶች) ጥገና ማስደረግ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያንሳር (ሊፍት) ጥገና የጨረታ ማስታወቂያ (GOV-2/2018)
የኦሮሚያ የህግ ማሠልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት በአዳማ ከተማ ከአባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል በስተምእራብ በኩል ባለው ዋና ጽ/ቤት ሕንፃ ውስጥ ያሉት ሁለት አንሳሮች (ሊፍቶች) ጥገና የአንዱን ዓመት ኮንትራት ውል በመፈራረም ሊፍቶችን ሰርቪስ በማድረግ፣ በመጠገን በቂ ልምድና ሙያ እንዲሁም መለዋውጫ ያላችሁ ድርጅቶች ለሊፍት ጥገና አንዱን ሊፍት በየወሩ ሰርቪስ የምታደርጉበትንና ብልሽት ሲያጋጥም የምታስተካከሉበትን ዋጋ በማቅረብ በአካል ቀርባችሁ በማየት እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበትን ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ለመንግሥት መ/ቤቶች እቃ ለማቅረብ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ዝርዝር ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሣተፍ የሚያስችል የአገር ውስጥ ገቢ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽገው እስከ 16ኛ ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን እስከ አራት ሰዓት ድረስ ይሆናል ማለት ነው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የችሎት አዳራሽ ተዘግቶ ወዲያውኑ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ (የጨረታ) ሰነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ የጨረታ ማስከበሪያ የኢት. ብር 3,000 (ሶስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን የእቃዎች ድምር ዋጋ 10% /አስር ፐርሰንት/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ የሥራ ዋስትና በማስያዝ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ህጋዊ ውል ይፈራረማል።
- በአሸናፊ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0221100770 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብት አለው።
የኦሮሚያ የሕግ ማሰልጠኛ እና ምርምር ኢንስቲትዩት /አዳማ/