Your cart is currently empty!
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መስሪያ ቤት ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ እንዲሁም ለቁጠባ መገንጠያ አስፓልት መንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 21, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከካፒታል በጀት ለኮሪደር ልማት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት 1 (አንድ) እንዲሁም ለቁጠባ መገንጠያ አስፓልት መንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት 2 (ሁለት) መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን።
- በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከገቢዎች የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት:: በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት/በጥቅል/ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11/02/2018 ዓ.ም እስከ 25/02/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖሰታ መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 26/2/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ26/02/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ ቢ/ቁጥር 508 በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04/ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ፈርሞ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ጨረታ ሰነዱ ጋር የመሥሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን