Your cart is currently empty!
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የሕክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የሕክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት ይፈልጋል። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርባ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድና የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ጤና እንክብካቤ እና አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 20000 በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሽያል እና አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ቴክኒካል በተለያዩ ፖስታዎች በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ሥራ አስፈጻሚ ከፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመከፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046329963 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል