የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ ኤሌከትሮኒክስ እና የመኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

 Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግንአ/11/2018

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት

  • የጽህፈት መሳሪያ፣
  • የጽዳት እቃ ፣
  • ኤሌከትሮኒክስ እና
  • የመኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

 ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደለ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) በላይ በመሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በግዥና ንብ አስቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብና በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታ ሠነዱ የተገለፀውን የመኪና ጎማ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር ፣ የጽህፈት መሳሪያ ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) የኤሌክትሮኒክስ ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) እና የጽዳት እቃ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ስም በመከፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን ሰነዳቸውን ደብረብርሃን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ብ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣
  9. መስሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት በጥቅል(በሎት) ነው።
  10. ግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11.  በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደብርብርሃን ከተማ አስተዳደር መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-637-56-10 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

ደ/ብርሃን