አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የአስፋልት ዊሪንግ ኮርስ እና አስፋልት ባይንደር ኮርስ/ Asphalt Mix/ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Government(Oct 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

Please click on this Link In order to Bid on the Electronic Government Procurement website

 https://production.egp.gov.et/egp/bids/all/tendering/637e643c-7a18-4814-98ef-89e57f02a4f9/open 

Invitation to Bid

የአስፋልት ዊሪንግ ኮርስ እና አስፋልት ባይንደር ኮርስ/ Asphalt Mix/ ግዥ

Procurement Reference No: AACRA-NCB-G-0005-2018-BID-Open
Procurement Category: Goods

Market Type: National
Procurement Method: Open

Procurement Classification Code: 

  • Code: 71000000
  • Title: Mining and oil and gas services
  • Code: 102000000
  • Title: Construction Maintenance equipment & accessories
  • Code: 12000000
  • Title: Chemicals including Bio Chemicals and Gas Materials
  • Code: 22000000
  • Title: Building and Construction Machinery and Accessories


Lot Information 

  • Object of Procurement: የአስፋልት ዊሪንግ ኮርስ እና አስፋልት ባይንደር ኮርስ/ Asphalt Mix/ ግዥ
  • Description: Not Available
  • Lot Number: 1
  • Clarification Request Deadline: Oct 25, 2025, 5:00:00 PM
  • Pre-Bid Conference Schedule: Not Applicable
  • Site Visit Schedule: Not Applicable
  • Bid Submission Deadline: Nov 1, 2025, 10:00:00 AM
  • Bid Opening Schedule: Nov 1, 2025, 10:30:00 AM

Eligibility Requirements
Participation Fee:  
Eligibility Documents: 

Financial Qualification

Factor Criteria
የፋይናንስ አቅም

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ለ) መሠረት ተጫራቹ የፋይናንስ አቅሙን የሚያሳዩ ሌሎች ማረጋገጫ ሰነዶች ሳያቀርብ ሲቀር፣

የጨረታ ዋጋ ዝርዝር ሠንጠረዥ

ተጫራቹ ያቀረበው የጨረታ ዋጋ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ አንቀጽ 12 መሠረት ካልሆነ፣

ዓመታዊ አማካይ የፋይናንስ ገቢው (turnover)

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ በተመለከተው መሠረት ተጫራቹ የሚያቀርበው የፋይናንስ መወዳደሪያ ሃሳብ መጠን በክፍል 3 የግምገማ ዘዴዎችና መስፈርቶች በተገለፀው መሠረት ከዓመታዊ አማካይ የፋይናንስ ገቢው (turnover) መብለጥ የለበትም፡፡

የመጫረቻ ገንዘብ

ተጫራቹ ለመጫረት ያቀረበው የመጫረቻ ገንዘብ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 13 ካልሆነ፣

የፋይናንስ አቅም

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ለ) መሠረት ተጫራቹ የፋይናንስ አቅሙን የሚያሳዩ ሌሎች ማረጋገጫ ሰነዶች ሳያቀርብ ሲቀር፣

ተጫራቹ ይህን ውል በተገቢው መንገድ ለማከናወን በቂ የሆነ የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ በሚያዘው መሠረት በክፍል 4 የተመለከተውን የተጫራቾች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ወይም ይህን ውል ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ የብድር ስምምነት ከታወቀ ባንክ ቢያንስ 50 ሚሊየን ብር በማቅረብ ማረጋገጥ ይኖርበታል ወይም የባንክ ስቴትመንት መግለጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

Legal Qualification

Factor Criteria
በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረ-ገፅ ላይ መመዝገብ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.7 መሠረት ተጫራቹ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረ-ገፅ ላይ ያልተመዘገበ ሲሆን፣ (የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ብቻ ይመለከታል)፣

የታደሰ የንግድ ፈቃድ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (i) መሠረት ተጫራቹ ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

የጥቅም ግጭት

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.3 መሠረት ከተጫራቹ ጋር የጥቅም ግጭት መኖሩ ሲታወቅ፣

ዜግነት

ተጫራቹ ከዜግነት አወሳሰን ጋር በተያያዘ በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.2 ላይ የተገለፀውን ካላሟላ፣ 

የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.1 መሠረት ጨረታው የቀረበው ከጋራ ማህበር ከሆነና ተጫራቹ የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ ማህበሩ የተቋቋመበትን ስምምነት ማቅረብ ካልቻለ፣

 

 

በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.4 መሠረት ከዚህ በፊት ከነበሩ የኮንትራት ግዴታዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ ተጫራች ከሆነ፣

የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ወይም የንግድ ፈቃድ

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ሐ) መሠረት የውጭ ሀገር ተጫራች ሆኖ ከተቋቋመበት ሀገር የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ወይም የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት ከታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

የተጨማሪ እሴት የምዝገባ ሰርቲፊኬት

በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (ii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የተጨማሪ እሴት ታከለ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣ 

Performance Qualification

Factor Criteria
Performance Qualification

1.     ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ውል ከፈረመ በኋላ ባሉት ተከታታይ በ5 /አምስት/ቀናት ውስጥ አቅርቦት ለመጀመር እንደሚችል የፅሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል በፅሁፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

2.     አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የእያንዳንዱን ሎት ቢያንስ በቀን 800 ቶን በቀንም ሆነ በማታ የስራ ሸፍት ማቅረብ ይኖርበታል እንደ አስፈላጊነቱ ፍላጎቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ባለስልጣን መ/ቤቱ በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት ከ800 ቶን በላይ በቀንም ሆነ በማታ የስራ ሸፍት ማዘዝ ይቻላል፡፡ ተጫራቹ ስምምነቱን በፅሁፍ ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት

3.     አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከገባ በኋላ በፕላንቱ ላይ በብልሽት በጥገና በመሳሰሉት ምክንያቶች ግዥ ፈፃሚው አቅርቦት እንዳይስተጓጎል ማድረግ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 

4.     ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጭነት ለሚያቀርበው ምርቱን ክብደት መጠኑ መለካት ያለበት ሲሆን በማምረቻ ቦታው የምድር ሚዛን ወይም Control Room print out ያለው መሆኑን በፅሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የምድር ሚዛን ወይም Control Room print out የሌለው ወይም የፅሁፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች በቴክኒክ ግምገማ ወቅት ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

Professional Qualification

Factor Criteria
መልካም ስራ አፈፃፀም

ማንኛውም ተጫራች ወይም አቅራቢ ላለፉት 2 ዓመታት ውስጥ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በአግባቡ ያልፈፀመው ውል ካለው ወይም በእያንዳንዱ በዚህ ጨረታ ባቀረበው ምርት ዓይነት ውል ኖሮት ደካማ የውል አፈፃፀም ያለው በግልግል ወይም የአስተዳደራዊ ዉሳኔ የተሰጠበት ተጫራች በዚህ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

Technical Qualification

Factor Criteria
በአምራቹ የተሰጠ የአቅራቢነት የስልጣን ደብዳቤ፣

በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 5.6 መሰረት በአምራቹ የተሰጠ የአቅራቢነት የስልጣን ደብዳቤ፣

በድርጅቱ የተሰጠ ዋስተና (Warranty)

በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 25 በድርጅቱ የተሰጠ ዋስተና (Warranty)፣

የቴክኒክ መግለጫ

በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 17 መሰረት የቴክኒክ መግለጫ ጽሑፍ፣

የዕቃ ወይም የአገልግሎቱ የምርት ሃገር

ተጫራቹ የጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ በሚፈቅደው መሠረት ዕቃውን  የሚያቀርበው ወይም አገልግሎቱን የሚሰጠው ከየት እንደሆነ ሳይገልጽ ሲቀር፣

requirement

የጨረታው አሸናፊ የሚያቀርበው ምርት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 በተገለፀው የቴክኒክ ዝርዝር ፍላጎት መግለጫ መሰረት የሚያሟላ መሆኑን ይኖርበታል፡፡ የሚያቀርበው ምርት ጥራት በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 የተቀመጠውን የጥራት መግለጫ (specification) መሰረት መሆኑን በፅሁፍ ያላረጋገጠ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ 

Technical requirement

1.     ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምርት የሚያቀርበው የአስፋልት ፕላንት ሰነድ በቀን 1000 ቶን እና ከዛ በላይ የማምረት አቅም እንዳለው ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ማሽኑ ካልብሬት የተደረገበት ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው እነዚህን ሰነዶች ማቅረብ ያልቻለ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

2.     ለአንድ ምርት ማቅረብ ያለበት የአስፋልት ፕላንት አንድ ሲሆን በሁለቱም ምርት ለመወዳዳር በቀን 1000 ቶን ማምረት የሚችል ሁለት ፕላንት ሊኖረው ይገባል፡፡ለዚህም የሰነድ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡

3.     ተጫራቹ የራሱ የሆነ የአስፋልት ማምረቻ ፕላንት ክሬሸርና የማምረቻ ኳሪ ሊኖረዉ ይገባል የባለቤትነት ማረገጋጫ ሰነድ ሊብሬ በውልና መስረጃ የተመዘገበ ውክልና ወይም ለዚህ ጨረታ የአቅርቦት ጊዜ የሚሸፍን የኪራይ ውል ለውል ዘመኑ የሰነድ ማረጋጋጫ ማቅረብ አለበት ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

 ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ውል ከፈረመ በኋላ ባሉት ተከታታይ በ5 /አምስት/ቀናት ውስጥ አቅርቦት ለመጀመር እንደሚችል የፅሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል በፅሁፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

Bid Security Amount: 500,000 ETB

Bid Security Form For MSE: Letter from Small and Micro Enterprise,

Bid Security From for Foreign Bidders: Bank Guarantee, CPO,

Notice: 

  • Terms and Conditions: The authority has the right to cancel the tender completely or partially

Address: 

  • Procuring Entity: Addis Ababa Road Authority
  • Country: Ethiopia
  • Town: Addiss ababa
  • Street: ፑሽኪን አደባባይ ሳርቤት
  • Room Number: 1st floor room no104
  • Telephone: +251 11 372 2815
  • Email: SoSiown4@gmail.com 
  • Po Box: 9206
  • Fax: 9206

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *