Your cart is currently empty!
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1500 ካሬ ሜትር የሆነ ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Be’kur(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሽ አቶ ዳንኤል አስማማው አስረስ እና አፈ/ተከሳሽ አቶ አቢዮት ዘለቀ አጉማስ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በተከሳሽ ሥም ተመዝግቦ የሚገኝ በአዋሳኝ በምሥራቅ እና በምዕራብ መንገድ፣ ካርታው ላይ ትርፍ ቦታ፣ በሰሜን መንገድ፣ ካርታው ላይ ትርፍ ቦታ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኝ 1500 ካሬ ሜትር ቦታ ግምቱ ብር 2,665,321.55 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ አንድ ብር ከሀምሳ አምስት ሳንቲም/ ቦታው የሊዝ ዕዳ ያለበት ሆኖ ህዳር 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በስዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን 1/4ኛውን በሞዴል 85 ወዲያውኑ ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያዝዛል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት