Your cart is currently empty!
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት 56.60 ካሬ ሜትር የሆነ ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Be’kur(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
በከሣሽ ይንገስ ጌታሁን ህፃን ቴዎድሮስ አይንዋጋ እና በተከሣሽ ዝይን ደርሰህ ህፃን እየሩሣሌም አይንዋጋ ዳግማዊት አይንዋጋ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በእነ ዝይን ደርሰህ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ካርታ ቁጥር አፄ/ቴ 9800/2015 ክ/ከ/ቀበሌ አዲስ አለም በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አዛለች ጌታሁን፣ በሰሜን አዝመራ ዘለቀ እንዲሁም በደቡብ ትልቅሰው አፈረ የሚያዋስነው 56.60 ካሬ ሜትር ቦታ በግምት መነሻ ዋጋ ብር 545,258.71/ አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከ71/100 ሣንቲም/ ሆኖ ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በስዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞዴል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት