Your cart is currently empty!
የቦታው ስፋት 135 ካ/ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አልማዝ ንጋቱ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ዘርዑ አብርሀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/148866 በ17/08/2015 ዓ/ም እና በመ/ቁጥር/153134 በ02/10/2015 ዓ/ም በ11/11/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 1457 የሚገኝ መኖሪያ ቤት እና ይዞታ በካ/ቁ/ቦሌ1/6/1/3/1210/9887/01 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት 135 ካ/ሜ ካርታ ያለው በሊዝ ይዞታ መኖሪያ የተመዘገበ ከላይ በተገለጸው ካርታ ቁጥር የተገለጸው ይዞታ በ2003 ዓ/ም አየር ካርታ መሰረት ከፊት ለፊት ያለውን ቤት በመንገድ ጥናት መሰረት 13 ካ/ሜ የሚቆርጠው ሲሆን በካርታ ደግሞ 4.72 ካ/ሜ ከፊት ለፊት ያለውን ቤት የሚቆርጠው በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 10,723,425 (አስር ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀያ ሦስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አምስት ብር) ሆኖ በጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቅያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ/ም ፍ/ቤቱ በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 2,680,856.25 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማኒያ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻፀም ጽ/ቤት