Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና የስትራቴጂ ልማት ጥናት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ የሥርዓተ–ፆታ እኩልነት እና የስትራቴጂ ልማት ጥናት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፡–
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል።
2. ተጫራቾች በዚህ የሥራ ዘርፍ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫትና የንግድ ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 10% (አስር ፐርሰንት) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
4. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት፡–
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒካል ዶከመንት ኦሪጅናልና ኮፒ እና አገልግሎት የሚሰጡበትን ዋጋ የያዘ ፋይናንሽያል ዶክመንት ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ17ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
5. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12
ስልክ ቁጥር፡-09-10-64-54-42
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ