በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የእንሰሳት ጤና ግብዓቶችን እና የድርቆሽ ማሰሪያ ቤለር ገመድ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 24, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የእንሰሳት ጤና ግብዓቶችን እና የድርቆሽ ማሰሪያ ቤለር ገመድ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ቁጥር እዓሀቢሮ 130/2018 የተለያዩ የእንሰሳት ጤና ላቦራቶሪ ምርመራ ኪት፣ የውጪ ጥገኛ ከመከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት የሚውል መገልገያ መሳሪያዎችን እና ቁሳቁሶች እና የድርቆሽ ማሰሪያ የቤለር ገመድ ግብዓቶች ግዥ

የእቃው ዝርዝር

  • ሎት1 : የእንሰሳት ጤና ላቦራቶሪ የምርመራ ኪት
  • ሎት 2 የውጪ ጥገኛ ከመከላከልና ቁጥጥር አገልግሎት የሚውል መገልገያ መሳሪያዎችን እና ቁሳቁሶች
  • ሎት 3 የድርቆሽ ማሰሪያ የበለር ገመድ
  • ሎት 4 የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻ ማሽን መለዋወጫ እቃዎች

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል 

1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የሚገዙ ግብዓቶች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 150.00 / አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

5. የመወዳያሪያ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የዋጋ ማቅረቢያ ፋይናሻል ፕሮፖዛል እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፤

7. ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ እቃውን አጠቃሎ ማስረከብ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ፣

8. ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ ማሸግ ያለብዎት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው፡፡

9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 4516 /058 220 6479 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – በስልክ ቁጥር 058 220 4516 ወይንም 058 220 6479
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ሃብት ቢሮ