Your cart is currently empty!
የቦታው ስፋት 154 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አልታዬ ገ/ዩርጊስ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ስፍራሽ በቀለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/193338 በ20/03/2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/201010 በ5/5/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቦታው ስፋት 154 ካ/ሜ የሆነ ቤትና ይዞታ በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,804,200 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ አራት ሺህ ሁለት መቶ ብር) ሆኖ በሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ እንደሚሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ በዕለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ12/10//2017 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 1,201,050 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አንድ ሺህ ሃምሳ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡ 30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገሊ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ንዝ በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስሎሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት