የቦታው ስፋት 380 ካ.ሜ. የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 24, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ ባለመብት ወ/ሮ ሀረጉ አብርሃ እና በፍ ባለዕዳ ወ/ሮ እንቁጣጣሽ አሰፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.115298 በ29/09/009 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ.121608 በ03/04/201ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በቀድሞው የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 በአዲሱ ለሚ ኩራ ከ ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ/1382 የካቁ የካ.9/1177582/04 የቦታ ስፋት 380 ካ.ሜ. የሐራጅ መነሻ 182,913.59 ( አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሶስት ብር ከ59/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *