Your cart is currently empty!
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ሴ/ር መ/ቤቶች ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ሴ/ር መ/ቤቶች ባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈለለች እና ክሊራንስ ከግብር መቤት ያቀረበ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል የምትችል፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
- የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በከፍል ከደ/ቤ/ወ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር /አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅሮብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ሻትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፤ ያለበለዚያ ያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ( ሃያ አንድ) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ስራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር፡- 09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47/09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት