Your cart is currently empty!
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የላብራቶሪ አገልግሎት ሳይቋረጥ አንዲሰጥ የጀኔሬተር ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ በወረዳው ጤና ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ማለትም ለደብረወርቅ፣ ቂጤና፣ ጊዜ ጤና ጣቢያዎች ላይ መብራት በሚጠፋበት ወቀት ለማህበረሰቡ የላብራቶሪ አገልግሎት ሳይቋረጥ አንዲሰጥ የጀኔሬተር ግዥ ከአቅራቢዎች በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈለለች እና ከሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል የምትችል፤
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፌደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለፀው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200) በመክፈል ከደ ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) አርጅና እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካ አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀርቡት ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል
- ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 9፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቾቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፣ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፦
1. ተጫራቾች የማህበሩ አባል ስለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ስራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
2 . የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ -የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር፡- 09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47/ 09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት