በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር የፅህፈት፣ የፅዳት፣ የህሙማን ማገገሚያ እና የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- 104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር ግዥ

ዴስክ ግ/ጨ C004/2018

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር መምሪያ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን

  • የፅህፈት፣
  • የፅዳት፣
  • የህሙማን ማገገሚያ እና የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በሚጫረቱባቸው የጨረታ አይነቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር  መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
  5. አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ያሸነፉትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ድረስ መቆየት ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የዕቃውን ሙሉ ስም፣ የተሰራበትን ሃገር እና የጥራት ደረጃውን (Specification) አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾቹ ስለሚጫረቱባቸው ለአያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የእቃውን አይነት ኤንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ኦሮሚያ መደበኛ ፖሊስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን በእለቱ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቡልቡላ ኦሮሚያ መደበኛ ፖሊስ ኮሌጅ ውስጥ በ5፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  10. የመጫረቻ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ከ15/02/2018 ዓ.ም እስከ 29/02/2018 ዓ.ም ድረስ ነው።
  11. የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር መምሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-63-61-99 80 ወይም 09-12-32-12-99 ይደውሉ።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *