Your cart is currently empty!
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪ (መኪናዎች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪ (መኪናዎች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- ደረጃ 3 (ሶስት) እና ከዚያ በላይ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ወይም በሚመለከታቸው ደረጃ የተሰጣቸው ጋራዦች (የተሻሻለ ደረጃን ያካትታል)፤
- በዘመኑ ታደሰ የኢንሹራንስ ሽፋን ሙሉ የጋራዥ ያላቸው ድርጅቶች፤
ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ | ሲፒኦ /CPO/ በማሰራት ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ወስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው/አስራ ስድስተኛው/ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-1-78-42-81 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ