Your cart is currently empty!
የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት Flanged bulk water meter and Traded bulk water meter በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን፡-
|
Lot |
Description of works |
Reference No. |
Categories of Required |
|
1 |
Flanged bulk water meter and Traded bulk water meter |
NCB/BTWSSSE/ GD/11/2018 |
Supplier of Goods
|
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ህጋዊ እና የታደሰ የ2018 ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 2% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሠርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ7ተኛ ቀን እስከ ቀኑ 8.00 ሰዓት ማስገባት እና ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክከል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Materia Devation) አይቻልም።
- ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት)ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬከተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልገሎት ድርጅት