Your cart is currently empty!
የቤ/ጉ/ክልል ፋይናንስ ቢሮ በመደበኛ በጀት ለክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
1. የቤ/ጉ/ክልል ፋይናንስ ቢሮ በመደበኛ በጀት ለክልሉ መንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ለተጫራቾች የተዘጋጀ መመሪያ፡–
2. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድርጅታቸውን ስም አድራሻ ሥልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማቸውንና ህጋዊ ማህተማቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው ባለስልጣን የተሰጠ ማረጋገጫ በቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸው ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
4. በጨረታ አሸናፊ የሚሆኑ ድርጅቶች በናሙናው እና እስፔስፊኬሹኑ መሰረት መሆኑ ተረጋግጦ በሚቀርበው ማስረጃ በቤኒሻኒጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 16 ድረስ በመምጣት ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ በውሉ አግባብ ክፍያዎች ይፈጻማሉ።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚወዳደሩበት ህትመት በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ሲፒኦ/ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተወዳደሩበትን በከፊል የሞሉትን ህትመት ዋጋ 3% በገንዘብ ተሰልቶ በማስቀመጥ እንዲሁም ሁሉንም ህትመቶች ከተወዳደሩ የሞሉትን ህትመት ዋጋ 3% የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘቡ 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ብር/ መብለጥ የሌለበት ሲሆን በፖስታ በማሸግ ቴክኒካል ኦርጅናል በፖስታው ውስጥ በግልጽ በሚታይ ጽሁፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብሎ በመፃፍና የድርጅቱን ስም፣ አድራሻና ማህተም በማድረግ በቴክኒካል ወይም ለብቻው ማቅረብ ይጠበቅበታል።
6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ከታወቁ እና ውል ከተፈራረሙ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ላሸነፉበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ውሉ ተፈጽሞ ሲጠናቀቅ የተያዘው የውል ዋስትና ገንዘብ ይመለሳል ውል ዋስትናው ፀንቶ የሚቆየው ለ3ወር መሆን አለበት፡፡ ሆኖ ግን እትሜትውን በመሉ ካስረከበ በኋላ ለ3ወር ሳይጠብቅ ሊመለስለት ይችላል።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤኒሻኒጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 16 በሚዘጋጀው ቦታ በይፋ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ በቤ/ጉ/ ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 16 ሆኖም የመክፈቻው የመጨረሻ ቀን በዓል ወይንም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሠዓት ለውጥ ሳይኖረው ይካሄዳል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 16 ድረስ በአካል በመምጣት መግዛት ይችላል።
9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 16 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ 057 775 0674 ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ደውሎ መረዳት ይችላሉ
የቤ/ጉ/ክልል ፋይናንስ ቢሮ