ጠቅላላ የቦታው ስፋት ከቀበሌ ቤት ጋር 170 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ ታደሰ ደበበ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ያሬድ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.273254 በ2/2/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.301864 በ16/4/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 በአሁኑ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወ12 ውስጥ የሚገኝ የቤ/ቁ 320 የሆነ በካታ ቁጥር ወ/12/ወዝ01/669/15271/0 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000091201251 በእነ አዳነች ሹሜ በርሄ ስም የተመዘገበ የተነጻጻሪ ካርታ ያለው ሲሆን የቤቱ ስፋት 41.2 ካ.ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 36.88 ካ.ሜ ጠቅላላ የቦታው ስፋት ከቀበሌ ቤት ጋር 170 ካ.ሜ የሆነ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,047,771.52 (ሶስት ሚሊዮን አርባ, ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አንድ ብር ከ52/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። በፌ/መ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.301864 02/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 428(1) መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ጨረታ 1/4ኛው 761,942.88( ሰባት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ብር ከ88/100) ሆኖ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን, ግምት ¼ ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አ/ጽ/ቤቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *