Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለከላላ ከተማ አስተዳደር ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
- ሎት 3 የጽዳት እቃ
- ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 (ደረሰኝ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ለየብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ወይም በተናጠል ሊሆን ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገቢዎች ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከለላ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914361759/0945488842 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ የሚያቀርቧቸው እቃዎች በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ እና ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መግባት አለባቸው እቃውንም ከዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ ስፔር ፓርት ውጭ በከለላ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ት⁄ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዘው ማምጣት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከለላ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለ ጀምሮ በሚቆይ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ4፡00 ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ።
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የእቃውን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, Electromechanical and Electronics cttx