Your cart is currently empty!
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
በአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ _የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡
6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት ፤ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000143426525 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናሉን ማስያዝ አለባቸው፡፡
8.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጥገና ጽ/ቤቱ ደ/ብርሃን መግዛት ይችላሉ፡፡
9.ማንኛውም ተጫራች የሞሉትን ዋጋ ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትበጥገና ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11 የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 011- 681-38-85 በመላክ ወይምቁጥር 011-681-30-66 ወይም 0913 189 073/0987 634 263 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት /ደብረ ብርሃን/