Your cart is currently empty!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 03 እና 10 ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/2018
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 03 እና 10 ለሚያሠራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ሥራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ተራ ቁጥር |
የፕሮጀከት ስም |
ወረዳ |
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
የተቋራጭ ደረጃ |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት |
አድራሻ |
|
ተቋራጭ |
||||||
|
1 |
ሰብ ቤዝ |
03 |
2%
|
ደረጃ 8 ተቋራጭ |
90 ቀን
|
ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ
|
|
2 |
ሰብ ቤዝ ብሎከ 30 |
10 |
ደረጃ 8 ተቋራጭ |
|||
|
3 |
ሰብ ቤዝ ብሎከ 31 |
10 |
ደረጃ 8 ተቋራጭ |
- ለሥራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2017 ዓ.ም የከፈሉ፤ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፣ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BiD SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 2 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት (work Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናውን (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር)ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ ፈ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16ኛው የሥራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሠራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (un balanced rate) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቋረጥ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ (Break down) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ወድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction)እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- በሥራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ሥራውን በነጻ እንደሚሠራ ይወሰዳል፡፡
- አጃቸው ላይ ምንም አይነት ሥራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሥራም ካላቸው 75% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡–
የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402
ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረተ ልማት ቡድን በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት