በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና የቢሮ የውበት /የጽዳት ዕቃዎች/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 26, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

በደ/////መንግሥት በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት ı እና ሎት 2 የተገለጹትን ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡

  • ሎት 1 የተለያዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች
  • ሎት 2 የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና የቢሮ የውበት /የጽዳት ዕቃዎች

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በመስኩ ሕጋዊ 2017/18 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
  2. በመስኩ የአቅራቢዎች የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በኢትዮ/ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ሰነዱን ከማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 28 በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና ድርጅቱ ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማሻ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 (አራት ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃ) ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የመንግስት የሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎቹን አጓጉዞ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ማሻ የመጀ//ሆስፒታል ማቅረብ አለበት።
  8. ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለበት።
  9. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ በስስክ ቁጥሮች 0910518389 ወይም 0917199383 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደ/////መንግሥት በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *