Your cart is currently empty!
ዘመን ባንክ አ.ማ. ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሐራጅ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለ) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ተ/ቁ | የተበዳሪው ስም | የአስያዡ ስም | የንብረቱ አድራሻ | የቦታው ስፋት በሜትር ካሬ | የካርታ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ | ሐራጅ የሚከናወንበት | የሐራጁ ደረጃ | ||||
| ከተማ | ወረዳ | የቤት.ቁ | ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታው ሰዓት | ||||||||
| 1 | ወይ አፎሚያ ታደለ ምንይዋብ | ወይ አፎሚያ ታደለ ምንይዋብ | አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ አራምሳ ሳይት | 10 | ብሎክ 434/የወለል ቁጥር 1ኛ የቤት ቁጥር B-434/11 | 37.16 ሜ.ካሬ | AA000061 0073044 340111 | ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ(መኖሪያ ቤት) | 2,220,634.51(ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከ51/100) | ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም | ጠዋት 3.30-5.00 | ጠዋት 5.00-5.50 | በድጋሚ | 
| 2 | አቶ ወግደረስ መራ እጅጉ | አቶ ወግደረስ መራ እጅጉ | አ.አ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ 1 ሳይት | 01 | ብሎክ 28/የወለል ቁጥር 04 የቤት ቁጥር B-28/30 | 30.31 ሜ.ካሬ | AA000080 104388280430 | ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ(መኖሪያ ቤት) | ብር 2,365,575.02(ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ሺ አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም) | ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም | ከሰዓት 7.30-9.00 | ከሰዓት 9.00-9.50 | በድጋሚ | 
| 3 | አቶ አቤል ሙሀመድ ይመር | አቶ አቤል ሙሀመድ ይመር | አ.አ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ገላን ሳይት | 04 | ብሎክ 159/ የወለል ቁጥር 01 የቤት ቁጥር B/159/12 | 30.31 ሜ.ካሬ | AA00007040 57111590112 | ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ(መኖሪያ ቤት) | ብር 2,056,606.61(ሁለት ሚሊዮን ሃምሳ ስድስት ሺ ስድስት መቶ ስድስት ብር ከ61/100) | ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም | ጠዋት 3.30-5.00 | ጠዋት 5.00-5.50 | በድጋሚ | 
| 4 | አቶ ግርማ ለገሰ ሚጀና | አቶ ግርማ ለገሰ ሚጀና | በሽገር ከተማ አስተዳደር ኮዪ ፈጩ ክ/ከተማ | 09 | ብሎክ 773/ የወለል ቁጥር 02/የቤት ቁጥር B/773-18 | 37.16 ሜ.ካሬ | OR00007 09022957 730218 | ኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ(መኖሪያ ቤት) | ብር 1,785,404,93(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አምስት ሺ አራት መቶ አራት ብር ከ93/100) | ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም | ከሰዓት 7.30-9.00 | ከሰዓት 9.00-9.50 | በድጋሚ | 
የሐራጅ ደንቦች፡–
- ተጫራቾች የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- አሸናፊው አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው::ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
- ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
- ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም የልማት ገንዘብ ክፍያ እና ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።
- የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል:: ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተቀመጡ ግዴታዎችን አያስቀርላቸውም።
- የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም::ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።
- ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል።
- የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ስንጋተራ በሚገኝው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጡትን ንብረቶች መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘመን ባንክ አ.ማ.
Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia