Your cart is currently empty!
ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ተ/ቁ | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | የንብረቱ አድራሻ | የቦታው ስፋት በሜትር ካሬ | የካርታ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ | ሐራጅ የሚከናወንበት | ||||
| ከተማ እና ክ/ከተማ | ወረዳ | የቤት.ቁ | ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታው ሰዓት | |||||||
| 1 | አቶ ደረጀ ሀብታሙ ዘለቀ እና ወ/ሮ ምስራቅ ጌታቸው ኃይሌ | አቶ ደረጀ ሀብታሙ ዘለቀ እና ወ/ሮ ምስራቅ ጌታቸው ኃይሌ | አ.አ የካ ክ/ከተማ | 05 | አዲስ | 678 ሜ.ካሬ | የካ/255409/13 | ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል 2B+G+3 ቤት | ብር 85,548,622.17( ሰማንያ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ስምንት ሺ ስድስት መቶ ሃያ ሁለት ብር ከ17/100) | ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም | ጠዋት 3.30-5.00 | ጠዋት 5.00-5.50 | 
የሐራጅ ደንቦች፡–
1. ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት (UnConditional Bank Guarente) በሀገር ውስጥ ባንኮች የተሰጠ የባንክ ዋስትና ሰነድ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
2. አሸናፊው የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው::አሸናፊው አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው::ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ሰነድ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ::
3. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና ሰነድ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው::
4. ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ፣ ያልተከፈለ የሊዝ ውዝፍ ክፍያን ጨምሮ ፣የንብረት ግብር ወዘተ ካለ እነዚህን ክፍያዎች በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል::
5. የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል:: ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተ.ቁ 2 ላይ የተቀመጠውን ግዴታ እና ሌሎች ግዴታዎችን አያስቀርላቸውም::
6. የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም:: ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል::
7. ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያ ገዥው ይከፍላል::
8. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሰንጋተራ በሚገኝው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18 ኛ ፎቅ ላይ ነው::
9. ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ንብረት መጎብኘት ይችላሉ::
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911 152 490 ወይም 0911 456 203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ዘመን ባንክ አ.ማ.
Mexico, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia