Your cart is currently empty!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የድርጅቱ ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 004/2018
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት የድርጅቱ ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ተሸከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡–
ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ፣በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2.የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5.ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
6.የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8.ጨረታው ከጥቅምት 16 ቀን 2018 እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ–ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ–ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ