የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 26, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በላይ የተጠቀሰው አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በውድድር መስፈርት መሠረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ በንግድ ፍቃድ፣ የአቅርቦት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 የስራ ቀናት ሆኖ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።

2. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በCPO ወይም ህጋዊ ባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ለ9ዐ ቀን ፀንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።

5. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ለ3 ወራት (90 ቀናት) ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።

7. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 ( አራት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ ከግዥ/ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።

8. ተጫራቾች በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 046 212 1455/ 046 212 2050

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *