Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ንብረት በግልጽ ሐራጅ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከተውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ በመሸጥ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ/ ዋስትና ሰጭ ስም |
ቤቱ የሚገኝበት |
የካርታ ቁጥር / የቁራሽ መሬት ልዩ መለያ ኮድ |
የቤቱ/ የቦታዉ አገልግሎት እና ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታ የሚካሄደበት |
|||
|
ከተማ |
ቀበሌ |
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
||||||
|
1 |
አቶ ጌታ ሙሉአለም ዉበቴ |
አቶ ጌታ ሙሉአለም ዉበቴ |
ባህርዳር |
ዳግ/ሚ/ክ/ከተማ |
AM00105420 2016 |
ለመኖሪያ ስፋቱ 200ካ.ሜ |
6,000,000 (ስድስት ሚሊዮን ብር) |
16/03/ 2018 ዓ.ም |
3፡30-5፡30 |
ኢ/ን/ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት ግቢ ውስጥ |
|
2 |
ሸጥቆላ ኤሌክትሮኒክስ እና የጽህፈት መሳሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ወ/ሮ ሙሉወርቅ አበባዉ ጣሰዉ |
ባህርዳር |
ዳግ/ሚ/ክ/ከተማ |
ዳ/ም/ክ/ከ/ 1212/2013 |
ለመኖሪያ ስፋቱ 100ካ.ሜ |
2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር) |
16/03/ 2018 ዓ.ም |
8-10 |
ኢ/ን/ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት ግቢ ውስጥ |
ማሳሰቢያ፤
1. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
2. ተጫራቾች በጨረታዉ ሰዓት እና ቦታ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ:: በጨረታው ወቅት ተበዳሪና ንብረት አስያዥ መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙም ጨረታዉ ይካሄዳል።
3. በዉክልና መጫረት የሚፈልጉ በወካይ ስም የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመግዛት የሚያስችል ግልጽ የዉክልና ማስረጃ ዋናዉን እና ኮፒ እንዲሁም ተወካዮችም ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ።
4. የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ የጨረታዉ ዉጤት በባህርዳር ዲስትሪክት ጨረታ ኮሚቴ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ ባንኩ የጨረታ አሸናፊዉን በጽሁፍ ሲያሳዉቅ ነዉ።
5. የጨረታው አሸናፊ ጨረታዉን ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ በ15 ቀናት ዉስጥ ቤቱን ተጫርቶ የገዛበትን ዋጋ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።
6. በንብረቱ ላይ በህግ የተወሰኑ ከመንግስት የሚፈለጉ ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታዉ አሸናፊ ይከፍላል።
7. ጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን በ15 ቀናት ዉስጥ ካልከፈለ ጨረታዉ ፈርሶ ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘዉ ገንዘብ ይወረስበታል።
8. ስለንብረቱ ዝርዝር ሁኔታ ማወቅ የሚፈልግ ቤቱን በአካል በማየት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 9778 እና 058 320 8826 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል።
9. ባንኩ ጨረታዉን እና የጨረታዉን ዉጤት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት